Jump to content

ወፍ

ከውክፔዲያ
የ08:11, 13 ሜይ 2020 ዕትም (ከ宜蘭第一公民 (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ወፎች ወይም አዕዋፍ ክንፍ ያላቸው፣ ደመ ሞቃትየጀርባ አጥንት ያላቸው እና እንቁላል ጣይ የሆኑ የእንስሳት መደብ አባላት ናቸው። በምድራችን ላይ ከ10,000 በላይ የወፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። በዚህም ወፎች በአለማችን ብዙ ዝርያ ያላቸው ባለጀርባ አጥንት እንስሳት ያደርጋቸዋል። ወፎች ከመሬት ላይኛው ጫፍ (አርክቲክ) እስከ ደቡባዊ ጫፍ (አንታርክቲካ) ድረስ ባላው ቦታ ይኖራሉ። መጠናቸው ከ5 ሣ.ሜ. (ሁለት ኢንች) የምትረዝመው ትንሿ ወፍ እስከ 3 ሜትር (አስር ጫማ) የምትረዝመው ሰጎን ድረስ ይለያያል።

የወፍ ዝርያዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዳክዬ

ዳክዬ በአብዛኛው በጨዋማና በለጋ ውሃ ላይ የሚኖር የወፍ ዘር ነው። ዳክዬ በአማካኝ 6ኪሎ ይመዝናል።