ወፍ
Appearance
![](http://178.128.105.246/host-http-upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/b/bc/480px-Petroica_boodang_Meehan_Range_1_crop.jpg/200px-480px-Petroica_boodang_Meehan_Range_1_crop.jpg)
ወፎች ወይም አዕዋፍ ክንፍ ያላቸው፣ ደመ ሞቃት፣ የጀርባ አጥንት ያላቸው እና እንቁላል ጣይ የሆኑ የእንስሳት መደብ አባላት ናቸው። በምድራችን ላይ ከ10,000 በላይ የወፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። በዚህም ወፎች በአለማ��ን ብዙ ዝርያ ያላቸው ባለጀርባ አጥንት እንስሳት ያደርጋቸዋል። ወፎች ከመሬት ላይኛው ጫፍ (አርክቲክ) እስከ ደቡባዊ ጫፍ (አንታርክቲካ) ድረስ ባላው ቦታ ይኖራሉ። መጠናቸው ከ5 ሣ.ሜ. (ሁለት ኢንች) የምትረዝመው ትንሿ ወፍ እስከ 3 ሜትር (አስር ጫማ) የምትረዝመው ሰጎን ድረስ ይለያያል።
ዳክዬ በአብዛኛው በጨዋማና በለጋ ውሃ ላይ የሚኖር የወፍ ዘር ነው። ዳክዬ በአማካኝ 6ኪሎ ይመዝናል።