የስኮትላንድ ጋይሊክኛ
Appearance
![](http://178.128.105.246/cars-http-upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/a/af/ScotlandGaelicSpeakers2001.gif/280px-ScotlandGaelicSpeakers2001.gif)
የስኮትላንድ ጋይሊክኛ (Gàidhlig /ካሊክ/) በስኮትላንድ የሚነገር ቋንቋ ሲሆን የኬልቲክ ቋንቋዎች አባል ነው። አሁን በስኮትላንድ ውስጥ 60,000 ያሕል ተናጋሪዎች አሉ፤ ይህም ከሕዝቡ ብዛት 1 ከመቶ ብቻ ነው።
ቋንቋው ከአይርላንድኛ ጋር ቅርብ ዝምድና አለው። ዛሬ ግን አብዛኛው የስኮትላንድ ኗሪዎች እንግሊዝኛ (በተለይ ስኮትኛ) ይናገራሉ።